- ደንበኞች የሚያገኙት የሕግ አገልግሎቶች በስነ ምግባር በፍጥነት በጥራት እንዲሁም በፍጥነት እንዲሆን የቻልነዉን ሁሉ ለማድረግ የሕግ ግዴታ አለብን።
- በልዩነት ነጻ የሕግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ሕጋዊ ምክር መስጠት የሚያስችል ሁኔታዎችን የምንከተል መሆናችን እንዳለ ሆነ ከዉል የመነጨ የሕግ ምክርና ልዩ ልዩ
አገልግሎቶችን ለማግኘት ግን ደንበኞች በመጀመሪያ ወደ ዌብ ሳይቱ በመግባት አባል በመሆን እና ወርሃዊ የስድስት ወር ወይም አመታዊ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
- ተመዝግበዉ ክፍያ እንደፈጸሙ የተረጋገጠ ደንበኛ ሆነዉ እዉቅና ያገኛሉ። ስለዚህም ለአገልግሎቱ ብቁ ይሆናሉ።
- የክፍያ አፈጻጸምና መጠን ፦ ለግለሰብ ደንበኞች የወርሃዊ ክፍያው በየወሩ 500 (አምስት መቶ) ብር ሲሆን ለተከታታይ ስድስት ወር የሚጸና
ደንበኝነት ከሆነ ደግሞ 2700 (ሁለት ሺ ሰባት መቶ) ብር ነዉ። አመታዊ ተመዝጋቢዎች በአንድ አመት የሚጸና አገልግሎት 4,800 (አራት ሺ ስምንት መቶ) ብር ነዉ። ደንበኛዉ
የቤተሰብ ጥቅልን የሚፈልግ ከሆነ ደግሞ በወር 600 (ስድስት መቶ) ብር በስድስት ወር 3,300 (ሶስት ሺ ሶስት መቶ) ብር እንዲሁም ለአንድ አመት የጸና አገልግሎት 6000
(ስድስት ሺ) ብር ይሆናል። ደንበኞቻችን የንግድ ተቋማት ወይም ድርጅቶች ከሆኑ ለወርሀዊ አገልግሎት 1000 (አንድ ሺህ) ብር ለስድስት ወራት የሚቆይ አገልግሎት ከሆነ ደግሞ
5400 (አምስት ሺ አራት መቶ) ብር ይሆናል። ለአመታዊ ተመዝጋቢ 9600 (ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ) ብር ነዉ።
የመጀመሪያ ዙር የአገልግሎት ክፍያ በምዝገባ ወቅት የሚከፈል ሲሆን ቀጣይ ክፍያዎች የመጀመሪያው የአገልግሎት ጊዜ ካበቃበት ቀን በኋላ ባሉት የ 7 ቀን ውስጥ መፈጸም አለበት።
ይህ ጊዜ ካለቀ በኋላ ያሉት 10 ቀናት የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሆኖ የሚቆጠር ሲሆን አገልግሎት ሰጪዉ ዉሉን የማቋረጥ መብት አለዉ።
- ከላይ የተገለጸው ደንብ ተፈጻሚ የሚሆነዉ ለሕግ ምክር አገልግሎት ብቻ ሲሆን ለዉል ለክስ ለመልስ ወይም ሌሎች የሕግ ሰነዶችን ለማዘጋጀት ደንበኛዉ ከአገልግሎት ሰጪዉ ጋር
በመነጋገር ተመጣጣኝ ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።
- የወርሃዊ ተመዝጋቢዎች በወሩ ውስጥ ባሉት ማናቸዉም የመደበኛ የስራ ቀናት 15 ሰዓታት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ሲሆን በቀን ውስጥ ለሁለት ጊዜ በመደወል
ለእያንዳንዳቸዉ 25 ደቂቃዎች መገልገል ይችላሉ። የስድስት ወር ተመዝጋቢ ደንበኞች ደግሞ 25 ወርሃዊ ሰዓታት በቀን ሁለት ጊዜ ለእያንዳንዳንዳቸወ 30 ደቂቃዎች ይገለገላሉ።
አመታዊ ተመዝጋቢዎች ደግሞ በወር ውስጥ ለ 30 ሰዓታት በቀን ሶስት ጊዜ በመደወል ለእያንዳንዳቸዉ 30 ደቂቃዎች አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ።
ደንበኞች ለአገልግሎት ሲደዉሉ በተቻለ መጠን ወዲያዉኑ የሕግ ምክር አገልግሎቱን የማግኘት መብት ያላቸዉ ሲሆን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ግን የሚጠበቀዉ አገልግሎት ከአንድ
ሰዓት እስከ 2 ሰዓት ዉስጥ የሚቀርብ ይሆናል። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ለተሻለ የአስቸኳይ ጉዳይ አፋጣኝ ምላሽ ለማግኘት በዌብ ሳይቱ የተዘጋጀ ሳጥንን ጨምሮ ከመደወል ዉጪ ባሉት
የመልክት ማስቀመጫ/መላኪያ አማራጮች (ቴሌግራም ኢ-ሜይል ፌስ ቡክ) ወይም መደበኛ ሞባይል የመልክት መላኪያ መንገድ መጠቀም ይችላል።
- ከላይ የተቀመጡት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ማናቸዉም ተመዝጋቢዎች ቀጠሮ ካስያዙ በኋላ በአካል ወደ ጠበቃዉ ቢሮ በመቅረብ በሳምንት ሁለት ጊዜ የአገልግሎት ተጠቃሚ መሆን
ይችላሉ።
- ማናቸዉም ደንበኞች በወር ወይም በአመት ውስጥ ያልተጠቀሙት የአገልግሎት ጊዜ ካለ የልዩ ልዩ ወጪዎች ተብሎ የተመደበዉን 30 ከመቶዉን ወደ ሚቀጥለዉ ወር ወይም አመት
ይሸጋገርላቸዋል። ነገር ግን ይህ የአገልግሎት ሽግግር ከሁለት ጊዜ በላይ ሊቀጥል አይችልም።
- ደንበኞች ያለባቸዉን ክፍያ ከፈጸሙ በማናቸዉም ጊዜ ዉላቸዉን ማቋረጥ ይችላሉ።
- ፍ/ቤት ካላዘዘ በስተቀር አገልግሎት ሰጪዉ በማናቸዉም ሁኔታ ያገኛቸዉን መረጃዎችና ማስረጃዎች ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ ያለመስጠት ግዴታ አለበት።
- አለመግባባቶች ስለሚፈቱበት ሁኔታ
በደንበኞችና በአገልግሎት ሰጪዉ መካከል አለመግባባቶች ቢፈጠሩ በመጀመሪያ በመግባባት ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ። ይህ ካልተሳካ ግን መደበኛ የአለመግባባት መፍቻ መንገዶችን
መጠቀም ይቻላል።
- የአገልግሎት ሰጪዉ አገልግሎት የጥብቅና ሙያን መሠረት ያደረገ በመሆኑ በጠበቆች ፈቃድ ምዝገባና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1246/2013 መሠረት የሚገዛ ይሆናል።
በአዋጅ ቁጥር 1246/2013 የሚሰራ